በዓለማችን ከኢትዮጵያ በስተቀር በድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ላይ የወንዙ አመንጪ ሆና ግዘፍ ሁለገብ ግድብ የሌለው ሀገር የለም።

የአባይ ጉዳዩ ግድብ መገደብና በኢኮኖሚ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይም ጭምር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን የሀገራችንን ሉዓላዊነት አሳልፈን የምንሰጥ ህዝቦች አይደለንም።

በዓለም አቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ታሪክ የላይኛው የተፋሰስ ሀገር ሆኖ (upstream country) በተለይ የወንዙ መነሻ ሀገር በራሱ ሉአላዊ ድንበር ውስጥ በወንዙ ላይ ለምገነባው ማንኛውም ነገር ከኢትዮጵያ ውጭ በአስገዳጅነት ይህን ማድረግ አለብህ ይህን ማድረግ የለብህም የተባለ እስከዛሬ አንድም ሀገር የለም። በተቃራኒው በድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ታሪክ የታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ሀገር ሆኖ፣ ከላይኛው የተፋሰስ ሀገር የሚመጣውን ውሃ በበላይነት መጠቀም አለብኝ ወይም ይህን ያህል የውሃ መጠን ይገባናል ያለ ከግብፅ በስተቀር በዓለም ላይ የለም፣ ታይቶም አይታወቅም።

በዓለማችን ከ286 በላይ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ይገኛሉ። በእነዚህም ወንዞች ላይ በርካታ ግድቦች ተገንብተው አግልግሎት ባመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በየትኛውም የሰው ልጅ ዘመን በኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ላይ የተፈፀመው እና እየተደረገ ያለው ተፅዕኖ በየትኛውም የድንበር ተሻጋሪ አህጉር/ሀገር አልተፈፀመም፤ የትኛውም የወንዙ መነሻ የላይኛው የተፋሰስ ሀገር እንደ ኢትዮጵያ የገዛ ወንዝን እንዳያለማ እና በወንዙ እንዳይጠቀም የተደረገ ወይም ጫና የተፈጠረበት ሀገር የለም።

በዓለማችን ከኢትዮጵያ በስተቀር በድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ላይ ግዘፍ ሁለገብ ግድብ የሌለው ሀገር የለም። በየትኛውም የድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ያላቸው ሀገራት ላይ ያልተፈፀመ ድርጊት ከድህነት ለመወጣት በምትጥረው ኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ተጽእኖ የሚደረግበት አንዳችም ምክንያት የለም።

በሀገራዊ፤አህጉራዊና አለማቀፋዊ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ የናሽናል ኦይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ጥላሁን በኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ሰፊና በጥናት የተደገፍ ገለጻና ማብራሪያን ያካተተ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡

 

 

 

 

Products and Services

 

 

Station Locator

Quick Contact

National Oil Ethiopia Plc
Airport Road Street
Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251116639494
Fax: +251116639495
P. O. Box: 951 code 1250
Email: info@noc.com.et

www.nocethiopia.com

Connect with us